የድሬዳዋ የከፍተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች አመታዊ የሻምፒዮና የእግር ኳስ ጨዋታ ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የድሬዳዋ የከፍተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች አመታዊ የሻምፒዮና የእግር ኳስ ጨዋታ ተጠናቀቀ
ድሬዳዋ ፤ የካቲት 22/2016(ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ አስተዳደር በ14 የከፍተኛ ዲቪዚዮን ክለቦች መካከል ሲካሄድ የሰነበተው አመታዊ የሻንፒዮና የእግርኳስ ጨዋታ ዛሬ ተጠናቀቀ ።
ከህዳር 16 ቀን 2016 ጀምሮ ከሶስት ወራት በላይ የተካሄደው የሻምፒዮና የእግር ኳስ ጨዋታ በመስቀለኛ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ዛሬ በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ መስቀለኛ 06 ህብረትን (ደቻቱን) አራት ለባዶ በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
በፍጻሜው የጨዋታ ስነ ስርአት ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የካቢኔ አባላት፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አሰልጣኞችና ተጫዋቾችና የስፖርት ቤተሰቦች ታድመዋል።