የኢትዮ- ማልታ የመጀመሪያው ቢዝነስ ፎረም በቀጣይ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮ- ማልታ የመጀመሪያው ቢዝነስ ፎረም በቀጣይ ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ የካቲት 22/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮ-ማልታ የመጀመሪያው ቢዝነስ ፎረም በቀጣይ ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።
የንግድ ፎረሙን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በኢትዮጵያ የማልታ ኢምባሲ እና የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በጋራ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ወይዘሮ ሀና አርዓያሥላሴ፣ ፎረሙ በኢትዮጵያና በማልታ መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ያላትን የንግድና የኢንቨስትመንት አመራጮች ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝም ገልጸዋል፡፡
መንግስት የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠሩን አስረድተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የማልታ አምባሳደር ሮናልድ ሚካሌፍ 40 የሚደርሱ የማልታ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች በፎረሙ እንደሚሳተፉ ተናግረዋል፡፡
በጤና፣ በአይሲቲ፣ በትምህርት፣ በኮንስትራክሽንና በሌሎች ዘርፎች ሰፊ ውይይቶች እንደሚደረጉም ጠቁመዋል፡፡