በድሬዳዋ ሐርላ የሚካሄደው ጥናትና ምርምር ለቱሪዝም እንዲጠቅም ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን - ኢዜአ አማርኛ
በድሬዳዋ ሐርላ የሚካሄደው ጥናትና ምርምር ለቱሪዝም እንዲጠቅም ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን
ድሬዳዋ፤ የካቲት21/2016 (ኢዜአ)፦የድሬዳዋ ሐርላ ቀበሌ የሚካሄደው የመካነ ቅርስ ጥናትና ምርምር ለቱሪዝም ዕድገት አበርክቶ እንዲኖረው የሚደረገው ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ገለጸ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ባገኘው ገንዘብ ዘመን የተሻገረው የድሬዳዋ የመንገደኞች የባቡር ጣቢያ ተርሚናል ቅርስነቱን በጠበቀ መንገድ እንዲጠገን የውል ስምምነት ድሬዳዋ ላይ መፈጸሙ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳሬይክተር ወይዘሮ ህይወት ሐይሉ ለኢዜአ እንደተናገሩት የአገሪቷ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶችን በመመዝገብ፣ በመጠበቅ፣ በመንከባከብና በማስተዳደር ለቱሪዝም ዕድገት እንዲውሉ እየተሠራ ይገኛል።
በድሬዳዋ የሚገኙትን የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ቅርሶችን ከድሬዳዋ አስተዳደርና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ተገቢው ጥበቃና ጥገና በማድረግ ምቹ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም የመካከለኛው ዘመን የንግድና የስልጣኔ ማዕከል በሆነችው ሐርላ ቀበሌ የሚካሄደው የመካነ ቅርስ ጥናትና ምርምር የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው የጠቀሱት።
በምርምር እየተገኙ ያሉ ሃብቶች ለአገር ሁለንተናዊ ዕድገት አበርክቶ እንዲኖራቸው ክትትል እየተደረገ መሆኑን በመግለፅ።
ሐርላን የጎበኙት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ተማም አወል(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በሐርላ ቀበሌ በተገነባው የማህበረሰብ ሙዚየምና በምርምር የተገኙ ውጤቶች አስተማሪና የትውልዱን የወል ታሪክ ለማነፅ የሚያግዙ ናቸው ።
እነዚህን ሃብቶች ማህበረሰቡ በባለቤትነት እንዲጠበቀውና ሙዚየሙ አጥር እንዲኖረው ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በሐርላ ቀበሌ በምርምርና በጥናት የተገኙትን ታሪካዊ ቅርሶችና ሙዚየሙ በተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና በዩኒቨርሲቲው ምሁራን መጎብኘታቸው ስፍራውን ይበልጥ እንዲታወቅና የቱሪዝም መዳረሻነቱ እንዲጎለብት ያግዛል ያሉት ደግሞ የድሬዳዋ የባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ ናቸው።
አቶ ሚካኤል እንዳሉት፤ አካባቢውን ምቹ የቱሪስቶች መዳረሻ የማድረግ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላ