የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በደብረብርሀን እና በአሰላ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ያሰለጠናቸውን መምህራን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ አስመርቀናል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2016(ኢዜአ)፦ ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በደብረብርሀን እና በአሰላ የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ያሰለጠናቸውን 1,658 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሁለገብ አዳራሽ አስመርቀናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።


 

ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለሁለት ዓመታት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ተመራቂዎቹ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት የሰለጠኑ መሆናቸውን አክለዋል።

ይህም አዲስ አበባ ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ ለማሳካት ትልቅ ሚና ያለው የትውልድ ግንባታችን አካል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም