ኢትዮጵያና ኬንያ የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመስራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና ኬንያ የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመስራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ኬንያ የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመስራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ ላደረጉላቸው ደማቅ አቀባበል አመስግነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሰፋ ያሉ ጉዳዮችን ያካተተው የዛሬው ውይይታችን የቆየውን ትስስራችንን ያጠናከረ ብቻ ሳይሆን የወደፊት ቁልፍ የትብብር መስኮችንም የለየ ነበር ብለዋል።
ኢትዮጵያና ኬንያ የጋራ አንድ ርዕይ እና እጣፈንታ እንዳላቸው ጎረቤቶች በጋራ ለመስራት ያለን ቁርጠኝነት ተጠናክሯል ሲሉም ገልጸዋል።