ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቀጣዩ የህዝብና ቤት ቆጠራ ዙሪያ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቀጣዩ የህዝብና ቤት ቆጠራ ዙሪያ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2016(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር ተገኝተው ቀጣዩን የህዝብና ቤት ቆጠራ በተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
በተደረገላቸው ገለጻም ቀጣዩ የህዝብና ቤት ቆጠራ የሶስት ዓመቱ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም አካል መሆኑ ተጠቅሷል።
ለህዝብና ቤት ቆጠራው የሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እንዲሁም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ውይይቱን ተከትሎም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የስራ መመሪያና አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የፕላንና ልማት ሚኒስቴርን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።