ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳንና ሱዳን ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 19/2016(ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያይተዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በከተማችን በዓለም ባንክ የሚደገፉ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ስለሚጠናቀቁበት እንዲሁም ቴክኒካል ድጋፎችን በዘላቂነት ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል።


 

ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን የመላው ጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያን ማስጎብኘታቸውንም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል።

እስከ አሁን ያከናወንናቸው የልማት ስራዎችን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙ እና ወደፊትም ይበልጥ ለመደገፍ ቃል በመግባታቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም