የኔዘርላንዱ ቢኤኤስኤፍ ድርጅት በኢትዮጵያ ለ4 ሺህ አርሶ አደሮች የአትክልት ምርጥ ዘሮችን ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኔዘርላንዱ ቢኤኤስኤፍ ድርጅት በኢትዮጵያ ለ4 ሺህ አርሶ አደሮች የአትክልት ምርጥ ዘሮችን ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፤ የካቲት 19/2016 (ኢዜአ)፦ የኔዘርላንዱ የአትክልት ምርጥ ዘር አምራች ድርጅት ቢኤኤስኤፍ ለ4 ሺህ አርሶ አደሮች የአትክልት ምርጥ ዘሮችን ድጋፍ አደረገ።
የኔዘርላንዱ የአትክልት ምርጥ ዘር አምራች ድርጅት ቢኤኤስኤፍ በትግራይ እና አማራ ክልሎች ለሚገኙ አራት ሺህ አርሶ አደሮች የአትክልት ምርጥ ዘሮችን ድጋፍ ዛሬ አድርጓል።
የተደረገው ድጋፍ በትግራይ እና አማራ ክልሎች በድርቅና በጦርነት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች ነው።
ቢኤኤስኤፍ ድጋፉን ኤስኤንቪ በተሰኘው የኔዘርላንድ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት አማካኝነት እንደሚያከፋፍል ተጠቁሟል።
የቢኤኤስኤፍ ድርጅት የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቤን ዴፕራተር ድጋፉን ለኤስኤንቪ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጁሊ ግርሃም አስረክበዋል።
ድጋፉ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርጥ ዘሮችን የሚያካትት ሲሆን 371 ሄክታር መሬት በዘር የሚሸፍን መሆኑ ተገልጿል።
ቢኤኤስኤፍ የተሰኘው ድርጅት በኔዘርላንድ መንግስት የሚደገፍ የአትክልት ምርጥ ዘሮች አምራች ድርጅት ነው።