ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደንቢዶሎ በረራዎችን መልሶ አስጀመረ

አዲስ አበባ ፤የካቲት 18/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደንቢዶሎ በሳምንት ሶስት ጊዜ በረራዎችን ዛሬ በደማቅ ስነ-ስርዓት መልሶ አስጀምሯል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን የሚገኘው የደምቢ ዶሎ አየር ማረፊያ ተቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ይህ በረራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ውስጥ የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የማስፋፋት አንዱ አካል መሆኑን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም