አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጡ - ኢዜአ አማርኛ
አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጡ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 18/2016(ኢዜአ)፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ለተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች በዛሬው ዕለት ሹመት ሰጥተዋል።
በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ አስር ኢብራሂም - የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፤
2. አቶ አልጀሊ ሙሳ - የክልሉ ሚዲያ ዋና ዳይሬክተር፤
3. አቶ ብርሀኑ አየሁ - የርዕሰ መስተዳድር የሕግ አማካሪ፤
4. አቶ በቀለ አንበሳ - የርዕሰ መሰተዳድር የኢኮኖሚ አማካሪ፤
5. አቶ አስማማው አብሾክ - የክልሉ ፍትህ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ፤
6. አቶ አብዱልከሪም ሙሳ - በክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፤
7. አቶ ሉቁማን አብዱልቃድር - የአካባቢ ደን ሀብት ጥበቃ አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን፤
8. አቶ ሁሴን ሀሰን - በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ፤
9. አቶ አህመድ ሙሳ - በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡