30 የህክምና ባለሞያዎች በኢትዮጵያ ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 17/2016(ኢዜአ)፦ 30 የህክምና ባለሞያዎች በኢትዮጵያ ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከፖላንድ የመጡት የህክምና ባለሞያዎች የማህፀን እና ፅንስ፣ ኒውሮሎጂ፣ ኒውሮሰርጀሪ እና የሰመመን ህክምና ባለሞያ መሆናቸውን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የህክምና ባለሞያዎቹ ለአስር ቀናት በኢትዮጵያ የሚቆዩ ሲሆን ከዛሬ የካቲት 17 እስከ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ በጦር ሀይሎች ሆስፒታል እና ሌሎች ተቋማት አገልግሎቱን ይሰጣሉ ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሆስፒታሎች በተጨማሪ ወደ አርባ ምንጭ በመጓዝም አግልግሎቱን እንደሚሰጡ ተመላክቷል።

የህክምና ባለሞያዎቹ በተከታታይ ሶስት አመት ለሶስተኛ ዙር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት አገልግሎቱን የሰጡ ሲሆን ቁጥራቸው በየአመቱ እየጨመረ መምጣቱም በመረጃው ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም