ለቀድሞዋ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የክብር ሽኝት ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ለቀድሞዋ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የክብር ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2016 (ኢዜአ)፦ ለቀድሞዋ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የክብር ሽኝት ተደረገላቸው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ ላለፉት 5 ዓመታት ከጤና ሚኒስትርነት በተጨማሪ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት የቦርድ አመራር ሆነው አገልግለዋል።
የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ሚኒስቴሪያል ሊደርሺፕ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ሆነው በቅርቡ ለተሾሙት ዶክተር ሊያ በዛሬው ዕለት የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በጋራ ላሳለፍናቸው 5 ስኬታማ ዓመታት፣ ለተገኙ ውጤቶችና ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅዖ ዛሬ ዶክተር ሊያን አመሰግነን በክብር ሸኝተናቸዋል ብለዋል ።
ዶክተር ሊያን በአዲሱ ሹመታቸው መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማቸውም ከልብ እመኛለሁ ሲሉም የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።