ዘላቂ የመሬት አጠቃቀምን የሚያበረታታ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
ዘላቂ የመሬት አጠቃቀምን የሚያበረታታ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2016(ኢዜአ)፦ ዘላቂ የመሬት አጠቃቀምን የሚያበረታታ የቴክኖሎጂ ፕሮጀክት በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይፋ ተደርጓል።
በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ከጃፓኑ ቶቶሪ ዩኒቨርሲቲ፣ ከግብርና ሚኒስቴር፣ከአማራ ክልል ግብርና ምርምር ተቋምና ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና ምሁራን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ዘላቂ የመሬት አጠቃቀምን (SLM) ለመዘርጋትና በረሃማነትን ለመዋጋት ቴክኖሎጂን መጠቀም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር የተደረገ ሲሆን ይህም ለመሬት አጠቃቀም ስራዎች አመቺነቱ በምርምር የተረጋገጠ መሆኑ ተመልክቷል።
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያና በጃፓን ተቋማት በትብብር ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነ ና ለስኬታማነቱ በትብብር መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።
የባህር ዳር እና ቶቶሪ ዩኒቨርስቲ ከዚህ ቀደም በተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት መሰረት በትብብር እየሰሩ የሚገኙና በዚሀም ቶቶሪ ዩኒቨርስቲ ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የትምህርት እድል እየሰጠ እንደሚገኝ ተመላክቷል
ሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች በተለይም በርሃማነትን ለመዋጋት የሚያስችል የጋራ ምርምር ሲያካሂዱ መቆየታቸውን በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።