ቀጥታ፡

አምባሳደር ጽጋብ ክበበው ከመንግስታት ድርጅትና ኦስትሪያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2016(ኢዜአ)፦በሲዊዘርላንድ ጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጽጋብ ክበበው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ኦስትሪያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ጽጋብ ከሥራ ኃላፊዎቹ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽና የትብብር መስኮች የተወያዩ ሲሆን ከዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ራፋኤል ማሪያኖ ግሮሲ ጋርም መክረዋል።

በሌላ ዜናም ከኦስትሪያው የአፍሪካ ክፍል፣ የአውሮፓና የዓለም አቀፍ ጉዳዮች የፌዴራል ሚኒስትር ከሆኑት ሮበርት ዚያች ጋር በኢትዮ-ኦስትሪያ የሁለትዮሽና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

አምባሳደር ጽጋብ ክበበው ቀጥለውም በመንግስታቱ ድርጅት የአደንዛዥ ዕጽና ወንጀል ቢሮ የፖሊሲ ትንተና እና የህዝብ ጉዳዮች ከፍል ዳይሬክተር ጂያን ሉክ ለማሃዩ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በልማት ፕሮጀክቶች ቀጣይነት፣ በኢትዮ-ኦስትሪያ እና በዓለም አቀፍ ተቋማት ትብብርና አጋርነቶች የሚጠናከሩባቸው ጉዳዮች መዳሰሳቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም