የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ሹመቶችን አጸደቀ - ኢዜአ አማርኛ
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ሹመቶችን አጸደቀ

ሐረር ፤ የካቲት 14/2016 (ኢዜአ)፡- የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጸደቀ።
የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ አዳዲስ ሹመቶችን አጽድቋል።
ምክር ቤቱ ያጸደቀው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረቡትን የካቢኔ አባላት ሹመት ነው።
በዚህም መሰረት፡-
ወይዘሮ ሮዛ ኡመር የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ
ወይዘሮ ኢክራም አብዱልቃድር የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ
አቶ አሰፋ ቶልቻ የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ
አቶ ኡስማኢል ዩስፍ የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ
ወይዘሮ ረምዚያ አብዱልሃብ የክልሉ ሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊ
አቶ ቶፊቅ መሀመድ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ
አቶ መሀመድ ያህያ የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ
አቶ ያሲን አብዱላሂ የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ
ወይዘሮ ደሊላ ዩስፍ የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ
አቶ አብዱማሊክ በከር የክልሉ ዋና ኦዲተር ሆነው ተሾመዋል።
እንዲሁም በምክትል አፈ ጉባዔ አሪፍ መሀመድ አማካኝነት የቀረቡት አቶ ጅብሪል መሀመድ የኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ወይዘሮ ፈቲያ ሳኒ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ ምክር ቤቱ ሹመትን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
ቀደም ሲልም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የቀረበውን የክልሉ መንግስት የ2016 በጀት ዓመት ስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ የምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባዔው ተጠናቋል።