ቀጥታ፡

ጃርሶ ዱጎ 75ኛው የጉጂ አባ ገዳ ሆኑ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2016 (ኢዜአ)፦ 75ኛው የጉጂ ኦሮሞ አባ ገዳ ስልጣን ርክክብ ተካሂዷል፡፡

ላለፉት 592 ዓመታት ሳይዛነፍ በቆየው የጉጂ ገዳ ሥርዓት መሰረት 75ኛው የጉጂ ገዳ "ባሊ" ከሀርሙፋ ወደ ሮባሌ ተሸጋግሯል።

ከየካቲት 6 ቀን 2016 ጀምሮ ባለፉት ቀናት ሲካሄዱ የነበሩት የሥርዓት ማቅናት መርሐ ግብሮች ከተጠናቀቁ በኋላ በዛሬው ዕለት 75ኛው የጉጂ አባ ገዳ ጃርሶ ዱጎ መሆናቸው ታውቋል።


 

በሌላ በኩል፤ በ75ኛው የጉጂ ገዳ ኦሮሞ የስልጣን ሽግግር ጃርሶ አጋ በዕድሜ ትንሹ አባገዳ ሆነው ከተመረጡት መካከል ሆነዋል።

በስልጣን ሽግግሩ ሮበሌ ከሀርሙፋ ሲረከብ ከሦስቱ የጉጂ ኦሮሞ ጎሳዎች ማለትም ኡራጋ፣ ሆኩ እና ማቲ አባገዳዎች መካከል ወጣቱ ጃርሶ አጋ የማቲ ጎሳን በመወከል ስልጣን ተረክበዋል።

አባታቸው አባገዳ ሆነው በማገልገላቸው፤ ስርዓቱ የሚፈቅድላቸው በመሆኑ ሊመረጡ መቻላቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።

75ኛው የጉጂ አባ ገዳ ጃርሶ ዱጎ ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት ሥልጣኑን ይዘው የሚቆዩ ሲሆን፤ እሳቸው የአገልግሎት ዘመናቸውን ሲያጠናቅቁ ለሚዘጋጁት 76ኛው አባ ገዳ ያስረክባሉ።

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም