ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2016(ኢዜአ)፦ አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ባደረበት ህመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ተገልጿል።

አንጋፋው ድምፃዊ ጌታቸው ካሳ ሀገሬን አትንኳት፣ ውብ አዲስ አበባ፣ ሳይሽ እሳሳለሁ፣ ክፈቺውና መስኮቱን፣ የከረመ ፍቅር፣ ትዝ ባለኝ ጊዜ በሚሉት እና በሌሎች ተወዳጅ ዘፈኖቹ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም