በኢትዮጵያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ(ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ(ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ የካቲት 12/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ(ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ የኢትዮጵያ ኢንቬስትመንት ሆልዲንግስ ቦርድ ኢትዮ ቴሌኮም ህዝባዊ ለመሆን ያለውን ዝግጁነት እና የካፒታል ማርኬት ባለስልጣን በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ወደ ስራ በማስገባት ላይ የደረሰበትን ደረጃ ገምግሟል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ(ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል ሲሉም አክለዋል።
ይኽ ለሀገራችን አጓጊ አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገልጸዋል።