የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን የተሳተፉት የኡጋንዳ እና የሞሪሽዬስ መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን የተሳተፉት የኡጋንዳ እና የሞሪሽዬስ መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2016 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ጉባኤን የተሳተፉት የኡጋንዳ እና የሞሪሽዬስ መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ተሳታፊ የነበሩ መሪዎች እና የልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በዚህም የኡጋንዳ እና የሞሪሽዬስ መሪዎች በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የክብር ሽኝት ተደርጎላቸው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።