በኢትዮጵያ፣ ቻይና እና ዩኤንአይዲኦ መካከል የሶስትዮሽ የትብብር ስምምነት ተፈረመ

245

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የልህቀት ማዕከላት ማቋቋሚያ የሦስትዮሽ ትብብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በኢትዮጵያ፣ በቻይና እና ዩኤንአይዲኦ መካከል ተፈርሟል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ የልህቀት ማዕከላት ማቋቋሚያ የሦስትዮሽ ትብብር የጋራ መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በኢትዮጵያ መንግስት፣ በቻይና መንግስት እና ዩኤንአይዲኦ መካከል መፈረሙን በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል።


 

በፈጠራ የታገዙ መፍትሄዎችን ለማስገኘት በሶስትዮሽ ትብብር ይፋ የተደረገው በኢትዮዽያ በግብርና፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በታዳሽ ኃይል፣በዲጂታላይዜሽን የልህቀት ማዕከላትን የመመስረት ስራ የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን እና የገጠር ነዋሪዎችን ሕይወት ለማሻሻል ልዩ ዕድል ይዞ መጥቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም