የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ለተመረጡት የሞሪታኒያ ፕሬዝደንት አሸኛኘት ተደረገላቸው - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ለተመረጡት የሞሪታኒያ ፕሬዝደንት አሸኛኘት ተደረገላቸው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ለተመረጡት የሞሪታኒያ ፕሬዝደንት ሞሃመድ ኡውልድ ጉዞዋኒ አሸኛኘት ተደረገላቸው።
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ተሳተፊ የነበሩ መሪዎች እና የልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ለተመረጡት የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ኡውልድ ጉዞዋኒ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የክብር ሽኝት ተደርጎላቸው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።