ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዩኤንአይዲኦ ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ለኢትዮጵያ የልማት ስራ ላላቸው የፀና ድጋፍ አመሰገኑ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዩኤንአይዲኦ ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ለኢትዮጵያ የልማት ስራ ላላቸው የፀና ድጋፍ አመሰገኑ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የዩኤንአይዲኦ ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ለኢትዮጵያ የልማት ስራ ላላቸው የፀና ድጋፍ አመሰገኑ።
በፈጠራ የታገዙ መፍትሄዎችን ለማስገኘት በሶስትዮሽ ትብብር ይፋ የተደረገው በኢትዮዽያ በግብርና፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በዲጂታላይዜሽን የልህቀት ማዕከላትን የመመስረት ስራ የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን እና የገጠር ነዋሪዎችን ሕይወት ለማሻሻል ልዩ ዕድል ይዞ መጥቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ለቻይና መንግስት እና ለዩኤንአይዲኦ በዚህ እጅግ አስፈላጊ ሃሳብ ላይ በመተባበራቸው ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ ብለዋል።
የዩኤንአይዲኦ ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ለኢትዮጵያ የልማት ስራ ላላቸው የፀና ድጋፍ በተለይ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ ሲሉም ገልጸዋል።