ቀጥታ፡

የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ለተመረጡት የሞሪታኒያ ፕሬዝዳንት የእንኳን ደስ አልዎት መርሃ-ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2016(ኢዜአ)፦ የሞሪታኒያው ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ኦውልድ ጉዙዋኒ ለመጪው አንድ ዓመት የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አልዎት መርሃ-ግብር ዛሬ ተካሂዷል።


 

በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በተካሄደው ስነ-ስርዓት ላይ የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ(ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ተገኝተዋል።

ተመራጩ ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ኦውልድ ጉዙዋኒ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለተደረገላቸው መስተንግዶ ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም