የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ተሳታፊ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ተሳታፊ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11/2016 (ኢዜአ)፦ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ተሳተፊ የነበሩ መሪዎች እና የልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።
በዚህም የሳሀራዊ አረብ ሪፐብሊክ እና ቻድ መሪዎች በቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ የክብር ሽኝት ተደርጎላቸው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።