የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ተሳታፊ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 11/2016(ኢዜአ)፦ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው 37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ መሪዎች እና የልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው።
በዚህም፤ የኮሞሮስ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መሪዎች በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የክብር ሽኝት ተደርጎላቸው ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።