የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ሚኒስትሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ሚኒስትሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 10/2016(ኢዜአ)፦የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና ሚኒስትሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ የቻድ የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ሰክሰስ ማስራ፣ የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሄሌና ሲሚዶ፣ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።
የዓድዋ የድል መታሰቢያ ድሉ ከተገኘ ከ128 ዓመታት በኋላ ከፍታውን በሚመጥን መልኩ መገንባቱ ለጎብኝዎች ተገልጿል።
በመታሰቢያውም የወቅቱ የኢትዮጵያ መሪዎች፣ የጦር ጀግኖች፣ ፈረሰኞች፣ የጦርነቱን አውድ የሚያሳይ ምስለ ምህዳርና ሌሎችም ሀውልት ተሰርቶላቸዋል።