ቀጥታ፡

የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም ሃብትና መስህቦቿን በተለያዩ አማራጮች ለዓለም የማስተዋወቅ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ቱሪዝም ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፤ የካቲት 9/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን እምቅ የቱሪዝም ሃብትና መስህቦቿን በተለያዩ አማራጮች ለዓለም የማስተዋወቅ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኮንፍረንስ አቅምና መስህቦቿን እያስተዋወቀ ነው።

የአፍሪካ መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በተገኙበት የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት የቡና ስርአትን ጨምሮ ሌሎችም መስህቦችን የሚያሳዩ ሁነቶች ቀርበዋል።


 

በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው በቱሪዝም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ አስተባባሪ ማስተዋል አስማረ፤ በሁነቱ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነትና የሁሉ መገኛነት የሚያመላክቱ የተለያዩ ማሳያዎች መቅረባቸውን ገልጸዋል።


 

በሁነቱ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ( ዶ/ር)  ሃሳብ አመንጭነት የለሙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በስፋት ማስተዋወቅ ተችሏል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ስብሰባዎችን በብቃት የማስተናገድ አቅሟንም ያሳየችበት አጋጣሚ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በርካታ እንግዶችም የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን ለመጎብኘት አወንታዊ ምላሽ እያሳዩ መሆኑን ነው አስተባባሪዋ የገለጹት።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም