ቀጥታ፡

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የ2024 የሕብረቱን መሪ ቃል አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2016 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የ2024 የሕብረቱን መሪ ቃል አፅድቋል።

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ 44ኛ መደበኛ ስብሰባ በአጀንዳነት ያቀረበውን የ2024ቱን የሕብረቱ መሪ ቃል  አጽድቋሉ።

መሪ ቃሉ "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የሕይወት ዘመን፣ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“  የሚል ነው።

የአፍሪካ ሕብረት 2024ትን የትምህርት ዓመት አድርጎ መሰየሙም ይታወቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም