ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዚምባቡዌ እና ደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከዚምባቡዌ እና ደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 9/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዚምባቡዌ እና ደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ጋር የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከአፍሪካ ኅብረት የመክፈቻ ስነስርዓት አስቀድሞ ከዚምባቡዌ እና ደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንቶች ጋር የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ጋርም የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ተመላክቷል።