ቀጥታ፡

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 9ኛውን የከተሞች ፎረም ለመታደም ወላይታ ሶዶ ተገኝተዋል

ሶዶ ፤ የካቲት 8/2016(ኢዜአ):-  የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች 9ኛውን የከተሞች ፎረም ለመታደም ወላይታ ሶዶ ከተማ ገቡ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ወላይታ ሶዶ የገቡት 9ኛውን የከተሞች ፎረም ለመታደም ነው።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወላይታ ሶዶ ሲገቡም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉና የዞኑ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቶ ተመስገን በነገው ዕለት የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በይፋ እንደሚከፍቱም ይጠበቃል። 

በወላይታ ሶዶ ከተማ ለሚካሄደው የ9ኛው የከተሞች ፎረም በቂ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ እንግዶች እየገቡ መሆኑም በዚሁ ጊዜ ተገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም