የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2016(ኢዜአ)፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስዋቲኒ አቻቸው ፎሊል ሻካንቱ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናከርበት፣ በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ማዕቀፍ በተመለከተ የልምድ ልውውጥ በሚደረግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
ሁለቱ ሀገሮች በመካከላቸው የንግድ ግኑኙነት ለመመስረት ከመግባባት መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
የልዑካን ቡድኑ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉብኝት ማድረጉንም በመረጃው ተመላክቷል።