የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤የካቲት 8/2016 (ኢዜአ):- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ ለልዑካን ቡድኑ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ሂደት ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
አክለውም የሽግግር ፍትህ እና ብሔራዊ ምክክር ሂደት ዝግጅቶች ያሉበትን ደረጃም አብራርተዋል።
በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።