ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ሉላ ደ ሲልቫ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለመ ውይይት አድርገዋል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2016(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ደ ሲልቫ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የፀና ወዳጅነትን የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ውይይት ማድረጋቸው ተገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጽሕፈት ቤታቸው በተካሄደ ይፋዊ የአቀባበል ስነስርዓት በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙትን የብራዝል ፕሬዝዳንት ሉላ ደ ሲልቫን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ከስድስት አሰርት አመታት በላይ የቆየው የኢትዮጵያ እና የብራዚል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዋና ማጠንጠኛው ንግድ ነው። 


 

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ሉላ ደ ሲልቫ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የፀና ወዳጅነትን የበለጠ ለማጠናከር የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ውይይት ማድረጋቸውም ተመላክቷል።
 
ለፕሬዝዳንት ሉላ ደ ሲልቫ ክብር ከተዘጋጀው የምሳ ግብዣ በኋላ ሁለቱ መሪዎች ለአካባቢ ጥበቃ ያላቸውን ቁርጠኝነት በሚያንፀባርቅ ብሎም ለቡና ባሕል ያላቸውን የጋራ አድናቆት በሚያሳይ ሁኔታ በአንድነት ፓርክ የቡና ችግኞችን ተክለዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም