ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከኖርዌይ የዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከኖርዌይ የልማት ሚኒስትር አኔ ቤዝ ቲቭነሪም ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ በደን ልማት፣ በትምህርት፣ በግብርና ዘርፍ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

አምባሳደር ታዬ ኖርዌይ በሁኔታዎች የማትቀየር የኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ገልፀዋል።

ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ጠንካራ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ሚኒስትሯ አኔ ቤዝ ቲቭነሪም ተናግረዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ሁለቱ ሀገራት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም