ቀጥታ፡

የኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ በማሸነፉ ምክትል ፕሬዝደንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መርሃግብር ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 7/2016 (ኢዜአ)፦ የኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ በማሸነፉ ምክትል ፕሬዝደንቱ አዲስ አበባ ሲገቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መርሃግብር ተደርጎላቸዋል።

የኮትዲቯር ብሄራዊ ቡድን 34ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ በአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ቲሞኮ ሚዬሊ ኮኔ የተመራ ልዑክ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለማቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የእንኳን ደስ አላችሁ መርሃግብር እንደተደረገላቸው ተገልጿል።


 

በመርሃግብሩ ላይ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለምና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከሀገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ጋር በመሆን የተዘጋጀውን የእንኳን ደስ አላችሁ ኬክ ቆረሳ ማከናወናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም