የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተመድ የልማት ፕሮግራም ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7/2016 (ኢዜአ)፡- የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ) ተወካይ ሳሙኤል ባይድ ዶው ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ በርካታ ሃብቶችን ማሰባሰብ እና መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
የተጀመረውን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በተለይ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ቴክኒካል ድጋፍ እንደሚያደርግ ተወካዩ ተናግረዋል።