የኢትዮጵያ እና ቱኒዚያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ እና ቱኒዚያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016(ኢዜአ)፦ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የቱኒዚያ አቻቸው ናቢል አሚር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተነጋግረዋል።
እየተካሄደ ካለው 44ኛው የአፍሪካ ሕብረት ሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ባደረጉት ውይይት፤ በሁሉም መድረኮች ተደጋግፈው ለመሥራት መስማማታቸው ተገልጿል።
የኢትዮ-ቱኒዚያ የጋራ የሚኒስትሮች ስብሰባ በተቻለ ፍጥነት እንዲካሄድ ከመግባባት መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ሁለቱም ሀገሮች በመርህ ላይ ተመሥርቶ የአፍሪካ አጀንዳ በጋራ ማራመድ እንዲቻልም ሚኒስትሮቹ መክረዋል።