የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2016(ኢዜአ)፦ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ቶቢያስ ናይቦ ጋር በጽህፈት ቤታቸዉ ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሯ በቀጣይ ሶስት አመታት የሚተገበረዉን እና ሰሞኑን ይፋ የሆነዉን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ይዘቶች አብራርተዋል።
አይ ኤም ኤፍ በዚህ ረገድ ያለዉን ልምድና የቴክኒክ አቅም ለኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች እንዲያካፍልም ዶክተር ፍጹም ጠይቀዋል፡፡
በኢኮኖሚ ስታትስቲክስ እንዲሁም በፐብሊክ ኢንቨስትመንት አስተዳደር ላይም የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ በትብብር ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል፡፡
የአለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ቶቢያስ ናይቦ በበኩላቸዉ ተቋሙ ያለዉን ልምድና ተሞክሮ በማካፈል የትብብር ስራዉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በዉይይታቸዉም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡