ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፋሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2016 (ኢዜአ)፡- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት በማውሳት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን በአባልነት እና በአስተናጋጅነት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃመት በበኩላቸው አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማቸው ደስታ ገልፀው፤ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ በተለይ፣ በአፍሪካ ፀጥታ እና መረጋጋትን በማስፈን ረገድ ያላትን ሚና ሊቀመንበሩ አድንቀው ይህው ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም