ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር እየተገነቡ ያሉ የልማት ስራዎችን  ጎበኙ

ባህር ዳር ፤ የካቲት 5/2016 (ኢዜአ)፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራር አባላት በባህር ዳር ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን  ጎበኙ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባህር ዳር ከተማ ለሚያስገነባው ቅርንጫፍ መስሪያ ቤትም የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። 


 

በጉብኝታቸውም በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን አዲሱን የአባይ ድልድይና የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየምን የማጠናቀቂያ ስራዎች ተመልክተዋል።

የባህር ዳር ስታዲየም የማጠናቀቂያ ስራዎች የፊፋና የካፍ ደረጃዎችን ባሟላ መልኩ እየተገነባ እንደሆነም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

በስታዲየሙ ከ54 ሺህ በላይ የመቀመጫ ወንበሮችን ለመግጠም የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ ተናግረዋል።


 

በጉብኝቱም ከአቶ ተመስገን ጥሩነህ በተጨማሪ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ሌሎች አመራሮች ትናንት  በክልሉ የልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ከክልሉ አመራር አባላት ጋር የንቅናቄ መድረክ ማካሄዳቸው ይታወሳል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም