የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ መረጃን በተመለከተ የኮሙኒኬሽንና የአድቮኬሲ ሥልጠና እየሠጠ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ መረጃን በተመለከተ የኮሙኒኬሽንና የአድቮኬሲ ሥልጠና እየሠጠ ነው
አዲስ አበባ፤ የካቲት 5/2016 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለተቋሙ እና ለአጋር ተቋማት ሠራተኞች የስታቲስቲክስ መረጃን በተመለከተ የኮሙኒኬሽንና የአድቮኬሲ ሥልጠና እየሠጠ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል በከር ሻሌ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ ሥልጠና ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ሥልጠናው በዘርፉ የባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት የዘርፉን አጠቃላይ ሥራዎች ለማቀላጠፍና ውጤታማ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው መርሀ ግብር የኖርዌይ ስታቫንገር ዩኒቨርሲቲ የመስኩ ምሁር በሆኑት ፕሮፌሰር ጆ ሮስሌን መነሻ ጽሁፍ ቀረቦ ውይይት ይደረግበታል።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህው ሥልጠና ለሦስት ቀናት ይቆያል ተብሏል።