በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ወርቅ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ - ኢዜአ አማርኛ
በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ወርቅ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 5/2016 (ኢዜአ):- በህገ- ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ወርቅ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከአንድ ተጠርጣሪ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪው ሊያዝ የቻለው አንድ ኪሎ ግራም ወርቅ በሻንጣ ውስጥ ደብቆ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሕገ-ወጥ መንገድ ከሀገር በማስወጣት ላይ እንዳለ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ጥብቅ ፍተሻ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እያተጣራበት እንደሚገኝ ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመላከታል።