የትኛውም አይነት የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድበን ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም በጋራ መቆም አለብን - ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ - ኢዜአ አማርኛ
የትኛውም አይነት የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድበን ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም በጋራ መቆም አለብን - ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2016(ኢዜአ)፦ የትኛውም አይነት የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድበን ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም በጋራ መቆም አለብን ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ ገለፁ።
ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ ሻንቆ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሰራተኞች "ከእዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ እያካሄዱት ባለው ስልጠና ላይ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ በርካታ ያልተነኩ ሃብቶች ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው፤ ይህን ወደ ልማት በመቀየር ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ለማዋል መስራት እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡
በመሆኑም የፖለቲካ አመለካከታችን ሳይገድበን ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም በጋራ መቆም አለብን ብለዋል፡፡
በመፍጠርና መፍጠን እሳቤ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እና ከነጠላ ትርክት ይልቅ አሰባሳቢ እና ገዥ ትርክት መገንባት ይገባልም ነው ያሉት፡፡
በተጨማሪም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን የተናገሩት ረዳት ፕሮፌሰር ምህረቱ፤ ለዚህ ደግሞ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው አንስተዋል፡፡