ቀጥታ፡

ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 6 ወራት 157 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶች ማምረት መቻሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና ባለፉት 6 ወራት 157 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉን አስታውቋል።

የኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ግምገማ በድሬዳዋ ተካሂዷል።

በመድረኩም ምርቶቹን በሀገር ውስጥ በማምረትና በመተካት ይወጣ የነበረን የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት መቻሉ ትልቅ እምርታ መሆኑ ተመላክቷል።


 

ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ92 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን በማምረት ቀዳሚውን ድርሻ እንደያዘ የተገለጸ ሲሆን አዳማ፤ አረርቲ፤ ደብረ ብርሀን እና ሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚከተሉ ተመላክቷል።

በዘርፉ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ካለፈው ሁለት አመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ብልጫ እንዳለውም ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከተቋቋመበት ግዜ አንስቶ ከ573 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ መቻሉም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም