ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሠራተኞች "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ስልጠና ማካሄድ ጀመሩ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሠራተኞች "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ ስልጠና ማካሄድ ጀመሩ፡፡

ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤትና በክልል የሚገኙ የተቋሙ የቅርንጫፍ ማስተባበሪያ  ሠራተኞች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡  

በስልጠናው ሀብት የመፍጠር ጉዟችን፤ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግሥት ሠራተኛው ሚና በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ውይይት ይካሄዳል፡፡  


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤  የስልጠናው ዋና ዓላማ በመንግስት ዋና ዋና የልማት እና የሰላም ማጽናት ስራዎች ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በሂደቱ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ ከልዩነት ይልቅ አብሮነትን በማጠናከር በጋራ መስራት እንደሚገባ ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ስልጠናው የተቋሙ ሰራተኞች ሀገርን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ሚናው የጎላ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም