ቀጥታ፡

አዲሱ ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያ አራት ዲ ሃቪላንድ Q400 ወይም B737 አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም አለው

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2016(ኢዜአ)፦ አዲሱ ጎዴ ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ አራት ዲ ሃቪላንድ Q400 ወይም B737 አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

አዲሱን የጎዴ ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡

አውሮፕላን ማረፊያው በ3500 ካሬ ስፋት ላይ ያረፈ መሆኑንም አየር መንገዱ ገልጿል።

አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ አራት ዲ ሃቪላንድ Q400 ወይም B737 አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም እንዳለውም አክሏል።

በተጨማሪም የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ የውሃ ማጠራቀሚያ፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችም ያካተተ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም