ቀጥታ፡

አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2016(ኢዜአ)፦ በጎዴ ከተማ የተገነባው የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ አዲስ የተገነባውን ኡጋዝ ሚራድ አውሮፕላን ማረፊያን ዛሬ ወደ ሥራ አስገብተናል ብለዋል።


 

በመልዕክታቸውም አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል እና አውሮፕላን ማረፊያ ፍትሐዊ የልማት ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ምቹ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ገልጸዋል።


 

አየር ማረፊያው በአንድ ጊዜ አራት ቦይንግ 737 አውሮፕላኖችን ማስተናገድ እንደሚችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የተርሚል ግንባታው ሶስት አመት የፈጀ ሲሆን የተሳፋሪዎችን ምቾት ለመጠበቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተደራጀ መሆኑም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም