የአድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያዊያን ዘመን የማይሽረው ታሪክ የተገነባበት ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 3/2016(ኢዜአ)፡- የአድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያዊያን ዘመን የማይሽረው ታሪክ የተገነባበት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአድዋ ድል መታሰቢያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር) ተመርቋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የአገራት አምባሳደሮች፣ አርበኞችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል።


 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በመርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የአድዋ ድል ታላቅነቱን በሚመጥን መልኩ መታሰቢያ ሳይቀመጥለትና ሳይዘከር እስካሁን መቆየቱን ገልጸዋል።

ከዚህም በመነሳት በጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ  ( ዶ/ር)  ሃሳብ አመንጭነት የኢትዮጵያዊያን ዘመን የማይሽረው ታሪክ ተገንብቷል ብለዋል።

በመሆኑም የአድዋ ድል መታሰቢያ ታላቅነቱን በሚመጥን መልኩ የተረሱትን በሚያስታውስና ጀግኖችን ለዘላለም በሚዘክር መልኩ የታሪክ አሻራ ተገንብቷል ነው ያሉት።

አዲስ አበባም የመላው ጥቁር ህዝቦች ትልቅ የታሪክ አሻራ ያረፈባት ከተማ ሆናለች ብለዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም