የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ይጫወታል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ ፤የካቲት 2/2016 ኢዜአ ፡- የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡
ጨዋታው ከ ቀኑ 10፡00 ላይ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ ሉካስ ሞሪፔ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል፡።
ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ 3 ለ 0 ማሸነፏ ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዛሬውን መልስ ጨዋታ ባጠቃላይ ውጤት ካሸነፈ ወደ ሶስተኛ ዙር የሚሸጋገር ይሆናል፡
ብሔራዊ ቡድኑ ለመልስ ጨዋታው በፕሪቶሪያ ዝግጅቱን ሲያደርግ መቆየቱን የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን መረጃ ያመለክታል።