ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ብሄራዊ ጥቅሞቿን ማስጠበቅ በምትችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ማስጠበቅ በምትችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

በብሪክስ ማዕቀፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኮሚቴ ሁለተኛ ስብሰባ ትላንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተካሂዷል።

ከተለያዩ የፌደራል ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያ ከብሪክስ ማዕቀፍ ባህል እና አሠራሮች ጋር ራሷን በቀላሉ በምታስተዋውቅበት እና ብሔራዊ ጥቅሞቿን ማስጠበቅ በምትችልባቸው መንገዶች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ተመላክቷል።

ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ የልማት አጋርነትን፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን እና የባለብዙ ወገን ግንኙነትን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥታ በንቃት እንደምትሰራም ተገልጿል።

የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኮሚቴው ተጠሪነት ለኢትዮጵያ የብሪክስ ብሔራዊ የሚኒስትሮች ኮሚቴ መሆኑንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም